Monday, July 1, 2013

Free our heroes

Furaat Org

የወልዲያ መስጂድ ሰላም ኮሚቴዎች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ተሰማ፡፡
የወልዲያ ሰላም መስጂድ ኮሚቴዎች ከትላንት ወዲያ ቅዳሜ በ 22/10/05 ከጸጥታ ቢሮ እና ከህገወጥ መጅሊስ አባላት በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ባደረጉት ስብሰባ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው እና ከአስራ አምስት ቀን በሗላ አዲስ ተመረጥን ላሉት መንግጅሊሶች እንዲያስረክቡ የፀጥታ ቢሮው ትእዛዝ ማስተላለፉን የ”FOH” ምንጮች ዘግበዋል፡፡
በተያያዘም በዛሬው እለት በወልዲያ ከተማ ተዘግቶ የነበረው የሰላም መስጂድ ቢሮ ለጊዚያዊነት እንዲከፈት ትእዛዝ መተላለፉን የ ”FOH” ምንጮች ጠቁመዋል ፡ ይህም ሊሆን የቻለው የንብረት ማሳወቅ እና የሰራተኞች ደመወዝ እንዲከፍሉ ብቻ እንዲሆነ ምንጮቻችን አክለው ገልጸዋል፡፡
ድል ፍትህ ለተጠማው የኢትዮያ ሙስሊም!!!

No comments:

Post a Comment