Tuesday, August 25, 2015

ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ እንዳይፈቱ እገዳ ተላለፈ

ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ከእስር እንዳይለቀቁ ታግደዋል፡፡


አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡ ነጻ የተባሉት አመራሮች ባለፈው አርብ ከእስር ይወጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም አሁን ድረስ እስር ቤት እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

http:/ www.zehabesha.com/amharic/archives/46143

ፂምም የለዎት?

 በሁሰን ከድር

እኚህ ሰውዬ የፌዴራል እስልምና ጉዳዮች ፕሬዚዳንት እንደሆኑ ዛሬ በወጣ መጽሔት ላይ አየሁ፡፡ ያለዛሬም አይቻቸው አላውቅም፡፡እማውቅበት እድሉም የለም፡፡ በኦርቶዶክስ ክርስትና ፓትርያርኩ ፂማቸው ተንዠርግጎ ሲታይ የሃይማኖት አባትነታቸው ጎልቶ ይታያል፡፡ የካቶሊኩም ቄስ ፂም ያላቸው ይመስለኛል፡፡ የአይሁድም ራባዮች ፂማቸው ጎልቶ ይታያል፡፡ ሰማያዊ ሃይማኖት ተከታይና መሪዎች ፂም አልባ ሆነው አይቼ አላውቅም፡፡
የሃይማኖት መሪዎች በሃይማኖት ትምህርት የላቁ ሆነው መገኘታቸው ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ዘመናዊ ትምህርት ካከሉበት የተሻለ ነው፡፡ የለ ጠልቄ አልግባ.... የመጅሊሱ መሪ ፂም አልባ የተፈጥሮ ይሆን? የተፈጥሮ ከሆነ ምንም አይደል ከሕዝብ ጋር የሚያደርጉትን መስተጋብር አይተን ከሿሚያቸው ጋር በማንጸር ሃሳባቸውን እንገመግማለን፡፡
ግን ፂማቸውን ሼቭ አስደርገው ከሆነ ቢሮ የሚገቡት የተመደቡበትን መስሪያ ቤት ሳያውቁት ቀርተው ይሆን?
በየጊዜው መንግሥት የሚሾምልን ጓዶች መቼም አንዳንድ ነገር አያጣቸውም፡፡ ህምም...
አላህ ያሳያችሁ መሪዎቻችንን እኛ ጭቁን ሕዝቦች ብንመርጥ ኖሮ .....