Monday, July 1, 2013

abusing court system in Ethiopia

==============
‹‹ጭልፍ››
==============
በኢትዮጲያ ፖለቲካዊ የፍርድ ሂደቶች ላይ ያለ ‘ፖለቲካ’
በአወል አሎ
ሰኞ ሰኔ 24/2005

ህጎችንና የፍትህ ተቋማትን ለጨቋኝ ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶች መጠቀም በጣም ከጥንት ጀምሮ የመጣ ልምድ ነው፡፡ ከሶቅራጥስ እስከ የናዝሬቱ እየሱስ(ዓ.ሰ)፣ ከፈረንሳዩ ቅዱስ ጆን እስከ አሜሪካዊዋ ሱዛን አንተኒ፣ ከደ/አፍሪካው ኔልሰን ማንደላ እስከ ኢትዮጵያዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ድረስ ፍርድ ቤቶች በወቅቱ ላሉት ባለሥልጣናት ፖለቲካዊ ጠላት ይሆናሉ ተብለው እንደስጋት የታዩአቸውን ሁሉ ለማስፈራራት፣ ለማጥቃት፣ ፀጥ ረጭ ለማሰኘት፣ ለስደት ለመዳረግ ብሎም ህይወት ለማጥፋት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹ፖለቲካዊ ፍርድ ቤት› በመባል ተለይቶ የምንሰማው ክስተት በምዕራቡ ወይም በምስራቁ እንዲሁም በአምባገነን ወይም በዴሞክራሲያዊ ሥርዓቶች ላይ ብቻ የታጠረ አይደለም፡፡ በሁለቱም ማለትም በዴሞክራሲያዊ እና በአምባገነናዊ መንግሥታት ሁሉ፣ ፍርድ ቤቶች በባህሪያቸው ግጭቶችን የሚወስኑት በማይቀለበሱ ፖለቲካዊ ወይም ርዕዮተ-ዓለማዊ ጉዳዮች መልኩ በመፈረጅ ነው፡፡ የፍርድ ሥርዓት ፋይዳ ‹‹ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትን›› በማስወገድ ፍትህን ለማረጋገጥ ነው ብለን ልንከራረር እንችል ይሆናል ነገር ግን እውነታው ያለው የዳኝነት ሥርዓት ለሥልጣን-ሽኩቻ በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ቦታዎች ውስጥ አንዱ ሆኖ መገኘቱ ላይ ነው፡፡

በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅት ገኖ ከነበረው ፅሁፍና የህግ እሳቤ ውስጥ የተቃርኖ ክርክር መነሻ አንዱ ‘ሊበራል ህጋዊነት/ሌጋሊዝም’ ይባል ነበር፡፡ በመሆኑም ጁዲዝ ሽክለር ሌጋሊዝም የነበረውን የአግላይ አገዛዝ ጭፍን ምኞት አጋልጠዋል፡፡ ሴትዮዋ ምንም እንኳን ሌጋሊዝም ‹‹ለመልካም ፖለቲካዊ አገዛዝ›› ያለውን ‹‹ትልቅ አስተዋፅዖ›› በውል ቢረዱም ሌጋሊዝም ዜጎችን በሚያጠቁ ህጎች ላይ የሚያሳየው ዝምታ በማንሳት ‹መደበኛ የፍትህ ሂደቱን› እንድትወቅሰው አድርጓታል፡፡ ሽክለር እንደሚሉት ሌጋሊዝም የሚመፃደቅበት የህጋዊነት መርህ በራሱ ‹‹አሰቃይ ህጎችን ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ በዜጎች ላይ በኃይል ይጭናል፡፡›› ለምሳሌ በደ/አፍሪካው አፓርታይድ የህጋዊነት መርሁ የዘር ልዩነት መኖሩን በህጋዊነት እና መደበኛ ፍትህ ስም ለፍትህ አካላት የህጋዊነት ማዕቀፍ ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ከዚህ በመነሳት ሽክለር የደመደሙት በፖለቲካዊ ግጭቶች ውሳኔ ውስጥ ዋናው ጥያቄ የፍትህ ሂደቱ ‹ህጋዊ ነው› ወይስ ‹ፖለቲካዊ› የሚለው ሣይሆን በፍርድ ሂደቶቹ ወቅት የተሳተፈው የፖለቲካ ሥርዓት ዓይነት ነው በማለት ነበር፡፡ በዚህ ድምዳሜ ላይ ተቃውሞ ሊኖር ቢችልም ስለፖለቲካዊ የፍርድ ሂደት የሴትዮዋ ጥቆማ የሚያሳየን ነገር ቢኖር በፍትህ ሂደት ውስጥ የተሳተፈውን አካል የፖለቲካ ባህሪይ ላይ ትኩረት እንደናደርግ ነው ይህም ማለት ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊና የለውጥ ፖለቲካ ወይም ጨቋኝ መሆኑን መለየት ማለት ነው፡፡ እኔም በኢትዮጲያ ውስጥ ያለውን የቅርብ ጊዜ ፖለቲካዊ የፍርድ ሂደቶች ላይ ያለ ‹ፖለቲካ›ን ልመረምር የፈለኩት በዚሁ መነፅር ነው፡፡

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ የህግ ማዕቀፎች ትግበራ ህገ-መንግሥቱንም ጨምሮ የገዢውን ተቀናቃኞች ሁሉ ማጥቂያ ስትራቴጃዊ መሣሪያ መሆናቸውን አሣይተዋል፡፡ ጀርመናዊው ዳኛ ኦቶ ኪርቸመር ስለፖቲካዊ የፍትህ ሂደት በሚያወሣው መፅሃፉ ላይ ‹የጥንት ፖለቲካዊ የፍትህ ሂደት›ን ገዢው ሥርዓት ለህዝብ ዕይታ ራሱን ከፖለቲካው ምህዳር ያገለለ በማስመሰል ጠላቴ ናቸው ብሎ ያሰባቸውን ሁሉ ለመቅጣት ይጠቀምበት እንደነበር አብራርቶ ፅፏል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያሉ ነውጦችን እና ለአብዮታዊ ተቃውሞ ያለውን ተጋላጭነት በማንሣት በፈጠራ ታሪክ ቅንብር ከመገናኛ ብዙኃን እስከ ውብና ህልማዊ በሆኑ የፖለቲካ መሣሪያዎች የታጠረች ሀገር- ኢትዮጲያ ለእውነትና ለፍትህ በቀጥታ ተቃራኒ የሆነ ፕሮጀክት ለማስፈፀም ለምን ፊቷን ወደ ፍትህ ተቋማት አዞረች? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡

ይቀጥላል..

የዋናውን ጽሁፍ ሙሉ ቅጂ በዚህ ሊንክ ያገኙታል፡፡
http://www.opendemocracy.net/awol-allo/politics-in-ethiopias-political-trials

No comments:

Post a Comment