Sunday, June 30, 2013

let's be heared our voice agaro

ድምጻችን ይሰማ አጋሮ
የሙስሊሙ ጥያቄ ሳይመለሰ ተቃዉሞን አቁሙ ማለት የማይታሰብ ነዉ ::
የአጋሮ ከተማ የአልአዝሐር መስጂድ ኢማምና የጂማ ዞን የመጅሊስ ሊቀመበር
አብዱል ሀሚድ አህመድ
አዎ በርግጥም የማይታሠብ ነዉ
ለእዉነት ንግግ የመስሚያ ጆሮ የሌለዉ ወያኔ አብድል ሀሚድ አህመድንም አልሰማዉም
እራሱ ለጂ ማዞን የመጅሊስ ሊቀመበርነት ሹሞት ሲያበቃ እዉነትን በመናገሩ ከስልጣን አባሮታል
የፍትህ ሬዲዮ በዛሬ ፕሮግራሞ እንደዘገበችዉ
አብዱል ሀሚድ አህመድ መንግስት ስልጣን ይብቃክ እዉነት ስሰማ ያንገሸግሸኛል ብሎታል
ይህ የሚያሳየዉ መንግስት የሾማቸዉ የመጅሊስ ባለስልጣኖች በስነ ምግባር ዱና ዉሸታም ሌቦች እንዲሆኑ ነዉ
የኢስላም ስረ መሠረቱን ለመናድ አይሁዳዉያን ከመሠሎቻቸዉ ገር ዘዉትር ይተባበራሉ ነገሩ ግን
የማያገኙትን ተመኙ
((ዩሪዱነ ሊዩጥፊኡ ኑረሏሂ በአፍዋሂሂም ወሏሁ ሙቲሙ ኑሪሂ ወለዉ ከሪህል ካፊሩን ))
በየዘመናቱ ኢስላም ላይ አደጋ ሲጋረጥ አሏህ የመረጣቸዉ ባሮቹ ሁለመናቸዉን በመስጠት ለኢስላም ዘብ እየቆሙለት ዛሬ ይህንን ዲን ለኛ አስረክቦናል
እኛ ስለአባቶቻችን ገድል እንደምናወራዉ ሁሉ ልጆቻችን ስለኛ ገድል እንጂ ዉርደትን እንዲያወሩ መፍቀድ የለብንም እኛ እናልፋለን ታርካችን ግን ዘላለም እንደማያልፍ ልንገነዘብ ይገባል
ስልጣንን ፈልገን ኢስላምን የምንዋጋ

በዚህም በዛኛዉም አለም ዉርደትን እንጂ ስልጣንን አናገኝም
ሞትን ፈርተን ወደኃላ የምንሸሽ ከሞት አናመልጥም
መታሠርን ፈርተን ከትግል የምንሸሽ የታሠሩት የበላይነትን ክብርን ሲጎናጸፉ እንጂ ሲዋረዱ ታርክ አላስተማረንም
ከዚህ ዉጭ ምንን ፈርት ወደኃላ መጪዉ ረመዷን ነዉ
አጋሮዎች ወደፊት
አልአዝሐር ዳግም በደመቀ ትክቢራ ትናጣለች inshala

No comments:

Post a Comment