Sunday, June 30, 2013

ምናባዊ ቃለ ምልልስ...!

ትግሉን ከሚነቅፍና የሙስሊሙ ችግሮች በመስጅድ ያልቃል ፣ መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም ከሚል አንድ ግለሰብ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፡፡ በተቻለ መጠን ሚዛናዊነቱን ለማስጠበቅ ጥረት ተደርጓል፡፡

ጤና ይስጥልኝ

ጤና ይስጥልኝ

(ስም ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም) የሙስሊሙን የመብት ትግል እንዴት ትመለከተዋለህ..?

የኢትዮጵያ ህዝቦች በኢህአዴግ ፋናወጊነት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግልና በከፈሉት መስዋዕትነት አስከፊውን የደርግ ስርዓት ገርስሰው በስራ ላይ ያለውን ህገ መንግስት ካጸደቁ በኋላ የመብት ትግል ብሎ ነገር የለም፡፡ ትግላችን ድህነትን ለማስወገድ ነው፡፡ ዋነኛ ጠላታችን ድህነታችን ነውና፡፡

ህገ መንግስቱ ሲጣስስ..?

ኢህአዴግ የከፈለው መስዋዕትነት ይሄን ህገ መንግስት ለማስጠበቅ ነው፡፡ ህገ መንግስቱ ተጥሶ ከተገኘ በግንባር ቀደምትነት የሚታገለው እራሱ ኢህአዴግ ነው፡፡

መንግስት በእምነት ጣልቃ ገብቶ ቢገኝ የህገ መንግስት ጥሰት መሆኑን ታምናለህ ?

በሚገባ!! መንግስት በእምነት ጣልቃ መግባት አይችልም::

ታድያ መንግስትህ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የእምነት ነጻነት ነፍጎ አንድን ሴክት ካልተቀበላችሁ እያለ ይገኛል፡፡ እንዴት ታየዋለህ...?

መንግስት እንዲህ አያደርግም፡፡ ማስረጃህ ምንድነው..?

ስልጠናው ሲካሄድ የነበረው በመንግስት ተቋማት ነበር፡፡ በሁሉም ስልጠናዎች ላይ ደግሞ የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ አሰልጣኙ ዶ/ር ሰሚር ደግሞ የቀ/ጠ/ሚ መለስ ዜናዊንና ዶ/ር ሽፈራውን አክብረው ስለጋበዙት አመስግኗል፡፡ ይሄ በቂ ማስረጃ አይሆንም..?
የመንግስት ተቋማት ግልጋሎታቸው ለህዝብ ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣናት ስልጠናው ላይ መገኘታቸው ስለ ህገመንግስቱ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሲሆን ዶ/ር ሰሚር ለሰጠው አስተያየት ግን መረጃው የለኝም፡፡

የመንግስት ተቋማት ሴኩላር ናቸው፡፡ ባለስልጣናቱም ተገኝተው ሲያስተምሩ የነበረው ስለ አንድ ሴክትና ( አህባሽ)ና ሌላውን ሴክት (ወሃብያን) ለማውገዝ ነበር፡፡ ዶ/ር ሰሚር አስተያየቱን የሰጠው በህዝብ ፊት በሂልተን ሆቴል በጋዜጣዊ መግለጫ ነበር፡፡

በዚህ ጉዳይ በቂ መረጃ ስላሌለኝ ይለፈኝ፡፡ ሆኖም መንግስት እንዲህ ያደርጋል የሚል እምነት የለኝም፡፡

እንግዲያውስ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት ሊያሳይ የሚችል ሌላ ማስረጃ ላቅርብ፡፡ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ታውቃቸዋለህ..?

አውቃቸዋለው፡፡ ሰዎቹ ጥሩ ቢሆኑም ከጀርባቸው ያሉ አካላት እነርሱን በመጠቀም ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ ቀውስ ሊከቷት በመሆኑ መንግስት ሰዎቹን በህግ መጠየቁ አግባብ ነው፡፡

ከመያዛቸው በፊት መንግስት አቅርቧቸው አወያይቷቸው ነበር፡፡ አሸባሪ ብሎ ለሚፈርጃቸው አካላትም አብሯቸው ለድርድር የተቀመጠውን መንግስትን አሸባሪ ብሎ መፈረጅ እንደሆነ አበክሮ ገልጾ ነበር፡፡ በኋላ ምን ተገኝቶ ነው መንግስት እራሱ በአደባባይ አሸባሪ ብሎ የፈረጃቸው..?

ዛሬ ሰላማዊ ከሆንክ ነገ ሽብርተኛ ስላለመሆንህ ዋስትና ነው እንዴ.. ዛሬ አሸባሪ የሆነም ነገ ሰላማዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ ሊደንቅህ አይገባም፡፡ ኦነግ ከኢህአዴግ ጋር አብሮ ጨቋኙን ደርግ ሲዋጋ ነበር፡፡ ያኔ ነጻ አውጪ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ሰላማዊ መንግስትን ሲወጋ አሸባሪ ይባላል፡፡ ይሄ ነው፡፡

መንግስት ነው ግለሰቦችን አሸባሪ ብሎ የሚፈርጀው ወይንስ ፍርድ ቤት...?

(ፈርጠም ብሎ) ፍርድ ቤት ነው-ንጂ!!

ታድያ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴው የቀረበበትን ክስ ክዶ በፍርድ ቤት እየተከራከረ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰዎች አሸባሪ ናቸው ተጠርጣሪ..?

ተጠርጣሪ

መንግስት ግን አሸባሪ ብሎ ፈርጇቸዋል፡፡

መንግስት እንደዚያ አያደርግም፡፡

‹‹ጂሀዳዊ ሀረካት›› ላይ አሸባሪ መሆናቸውን ከፍርድ ቤት በፊት ተፈርዶባቸው ተመልክተናል~!!

በእርግጥ ህዝብ ውዥንብር ውስጥ ሲገባና በመንግስት ላይ አለ አግባብ ወቀሳ ሲበዛበት ለህዝብ መረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይሄም አንዱ የአሰራር ግልጽነት ማሳያ ነው፡፡ ደግሞም ፊልሙ አስተማሪ ነበር፡፡

ሰዎቹ የቀረበባቸውን ክስ ክደው በፍርድ ቤት እየተከራከሩ ይገኛሉ፡፡ ኢቴቪ ደግሞ በአንደበታቸው ጥፋተኝነታቸውን ሲያምኑ ያሳያል፡፡ መረጃውን ለመቀበል ቶርች ተደርገዋል የሚባለውን አያረጋግጥልንም..? በህግ አንጻር ካየነው ደግሞ አንድ ግለሰብ በራሱ ላይ ያለመመስከር መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ በዚያ ላይ ፊልሙ ሲቀርብ የሰዎቹ ፈቃድ መጠየቅ እንዳለበት የሚዲያ ህጉ ይደነግጋል፡፡ ይሄ ሁላ የህግ ጥሰት የህግ የበላይነቱን ጥያቄ ውስጥ አያስገባውም..?

እ..እ..(ግንባራቸውን እያሻሹ) በእርግጥ ሰዎቹ በፊልሙ ላይ ተጠርጣሪ እንጂ ወንጀለኛ አልተባሉም፡፡ ማንኛውም የመብት ጥሰት ከተደረገ ግን በህግ የመጠየቅና ጥፋት የፈጸሙ አካላትን የማስቀጣት ሙሉ መብት አላቸው፡፡

ተበዳዮቹ ከሰው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ክሳቸውን ሳይመለከት ውድቅ አድርጎባቸዋል፡፡

እንደዚህ አይደረግም!!

በእርግጥም ተደርጓል!!

ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ

ውጤቱ ግን ግልጽ ነው፡፡

አልተቋጨም... ይቀጥላል...

No comments:

Post a Comment