Tuesday, June 25, 2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የኖርዌይ ቻፕተር በኦስሎ ከተማ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የኖርዌይ ቻፕተር ጠቅላላ ህዝባዊ ስብሰባውን ሰኔ-15, 2005 
ዓ.ም (ጁን 22 ቀን 2013 ) ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት ታሪካዊና 
ስኬታማ የሆነ ህዝባዊ ስብሰባ አደረገ። በእለቱም በተጋባዥ እንግድነት አቶ ሰለሺ ጥላሁን የሽግግር ምክር 
ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ፣ ሚስተር አዳም ዊስ በአውሮፓ የግለሰብ መብት አማካሪ ማእከል ዋና ዳይሬክተር 
ደራሲና ገጣሚ አቶ አበራ ለማ እንዲሁም በኖርዌይ የሽግግር ምክር ቤት የዲፕሎማቲክ ተጠሪ ዶ/ር 
ግሩም ዘለቀ ተገኝተው ነበር። 
ፕሮግራሙ የተጀመረው በ ዶ/ር ግሩም ዘለቀ የመክፈቻ ንግግር ሲሆን ፣ ስደተኞችንና ዲፕሎማሲን 
አስመልክቶ አጭር ገለጻ በማድረግና ተጋባዥ እንግዶችን በማስተዋወቅ ስብሰባው ክፍት እንደሆነና 
ታዳሚዎችም ማብራራዎችን ተከትሎ ጥያቄዎቻቸውን እና አስተያየቶቻቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ 
አስገንዝበዋል።
 በመቀጠልም ሚስተር አዳም ዊስ ስለ ጥገኝነትና ተከታትለው ስለሚመጡ የመብት 
ጥያቄዎች ማብራሪያ አድርገው ኢትዮጲያውያን በኖርዌይ ተደራጅተው ለሰብአዊ መብት ፍርድ ቤት 
ያስገቡትን የጥገኝነት ጥያቄ ክስ በተመለከተም ያሉበትን ሁኔታ አስረድተዋል። ከተሳታፊዎችም ለተነሱ 
ጥያቄዎች አንድ በ አንድ መልስ ሰጥተዋል።
 ደራሲ አቶ አበራ ለማ ከስራዎቻችው መካከል ጥቂቱን ለታዳሚው ያቀረቡ ሲሆን ፣ ኢትዮጵያና 
የኢትዮጵያዊነትን ስሜት የሚቀሰቅሱ ወቅታዊ ግጥሞች በአማርኛና በኖርዌጅያን ቋንቋ አሰምተዋል። 
በመቀጠልም፤ የሽግግር ምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ፤ አቶ ሰለሺ ጥላሁን ስለ ሽግግር ምክር ቤቱ ምንነት፤
አላማውንና የወደፊት አቅጣጫውን አስመልክቶ በሚከተሉት አብይ እርሶች ላይ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። 
  • የግፍ አገዛዝን ለማስወገድ ያሉን 5 አማራጮች
  • የምክር ቤቱ የቅድመ ምስረታ ሂደት
  • የምክር ቤቱ የምስረታ ጉባኤ
  • የምክር ቤቱ ድህረ ምስረታ እንቅስቃሴዎች
  • ለወገኖቻችን በአለም ዙርያ እንቁም
  • ስለሽግግር አሁን መነጋገር ለምን አስፈለገ?
  • ስርአቱን ሰለማስወገድና በሁሉ ሁሉ አቀፍ የሽግግር መንግስት ስለመተካት በዋሽንግተን ዲሲ ከጁላይ 2-5/ 2013 ስለሚደረግ ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ።
ከማብራሪያዎች በሗላ ሰፋ ያለ የጥያቄና መልስ ፕሮግራም የነበረ ሲሆን፣ ከታዳሚዎች ለቀረቡ 
ጥያቄዎችም፤ አቶ ሰለሺ ጥላሁን አንድ በአንድ መልስ ሰጥተዋል። በቀረቡት ማብራሪያዎች የተደሰቱ 
34 አዲስ አባላቶች የአባልነት ፎርም በመሙላት የኖርዌይ ቻፕተርን ተቀላቅለዋል። 
ህዝባዊው ስብሰባ ከተጠናቀቀ በሗላ አቶ ስለሺ ጥላሁን ከነባርና አዳዲስ አባለቶች ጋር አጠር ያለ 
ስብሰባ በማድረግና በህገ ደንቡ መሰረት ያባላትን መብትና ግዴታ ማበራሪያ በመስጠት፤ ቻፕተሩን 
የማጠናከርና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አዳዲስ የኮሚቴ አመራር አባላት ምርጫ የተካሄደ ሲሆን፣ 
በምርጫውም የሚከተሉትን አስራ አምስት አስተባባሪ አባላቶችን አፅድቛል፤ 

አቶ እንግዱ ወርቁ ፣ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ ፣ አቶ አዲስ ማሞ፣ አቶ ንጉስ ቱሉ፣ ወ/ሪት ሄለን ደሬሳ ፣ አቶ 
ናኦድ ከበደ፣ ወ/ሪት ፍቅርተ ነጋሳ፣ አቶ አርጋው ከበደ፣ ዶ/ር ግሩም ዘለቀ፣ አቶ ዮሃንስ ልኡል፣ አቶ 
ስብሃት አማረ፣ ወ/ሮ እመቤት ካሳሁን ፣ ወ/ሪት መሰለች ቸርነት፣አቶ አንዋር ሃሩን እና ወ/ሪት ሃና 
ሲሆኑ ። 
በመጨረሻም፤ በሊቀመንበርነት ዶ/ር ግሩም ዘለቀን፣ በ ዋና ፀሀፊነት አቶ ናኦድ ከበደን፣ በገንዘብ 
ያዥነት ወ/ሪት ሄለን ደሬሳን በመምረጥ ታርካዊው የኖርዌይ ቻፕተር ስብሰባ በስኬት ተጠናቛል። 
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
የኖርዌይ ቻፕተር!

No comments:

Post a Comment