Sunday, June 30, 2013

ትግላችን የሚሊዮኖች መሆኑን የሚያሳይ ቪዲዮ አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ አሳየ፡፡
ቅዳሜ ሰኔ 23/2005

ፍ/ቤቱ አቃቤ ሕግን ጊዜ በመስጠትም ጭምር እየረዳው ነው

በዚህ ባገባደድነው ሳምንት በቀጠሮ ድጋሚ በተዘጋው የመሪዎቻችን ችሎት አቃቤ ሕግ የትግሉን ሕዝባዊነት የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ለፍ/ቤት አሳይቷል፡፡ ለጥቂት ቀናት ብቻ በቆየው ችሎት አቃቤ ሕግ ከዩቲዩብ ላይ የሰበሰባቸውን ቪዲዮዎች ያሳየ ሲሆን በቪዲዮዎቹም የሙስሊሙ ህብረተሰብ ትግል እና ተጋድሎ ሕዝባዊነትን የተላበሰ መሆኑ ታይቷል፡፡ እንደ ፍ/ቤት ምንጮች በችሎቱ አቃቤ ሕግ ካሳያቸው ቪዲዮዎች መካከል ባለፈው አመት በታላቁ አንዋር መስጊድ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ የሚገኝበት ሲሆን የተቃውሞውን መጠናቀቅ ተከትሎም በርካታ ሕዝበ ሙስሊም ወደ ፒያሳ፣ መርካቶና አውቶብስ ተራ አቅጣጫ ሲተም የሚታይ ሲሆን የህዝቡ ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑ ተልክቷል፡፡

አቃቤ ሕግ የኮሚቴ አባላትን የአወሊያ መስጊድ ንግግሮችም በቪዲዮ መልክ ያቀረበ ሲሆን በንግግራቸውም ሕዝበ ሙስሊሙ እየደረሰበት ያለውን በደል ለህዝቡ በገለጻ መልኩ ሲዘረዝሩ ይታያል፡፡ በተጨማሪም የአሕባሽን አስከፊነት የሚያሳይ፣ የመንግስትን ጣልቃ ገብነት የሚያስገነዝቡ ቪዲዮዎች መቅረባቸው የታወቀ ሲሆን ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ሐምሌ 6 የመንግስት ሀይሎች አወሊያ መስጊድ ገብተው ሰላማዊው ህዝብ ላይ የፈጸሙትን አሳፋሪ ድርጊት ያጋለጸበት የቢ.ቢ.ኤን ሬዲዮ ፕሮግራምም ለፍርድ ቤቱ ተደምጧል፡፡

አቃቤ ሕግ እስከ አሁን ለመንግስታዊው ፍ/ቤት ባቀረባቸው የምስክርም ሆነ የሰነድ ማስረጃዎች በአብዛኛው በጭብጥ ደረጃ የመንግስትን ክስ ከማጠናከር ይልቅ በተቃራኒው የመሪዎቻችንን ነጹህነትም ሆነ የህዝቡን ሰላማዊነት የሚያመላክትና በተቃራኒው ሰነዶቹ ለመሪዎቻችን መከላከያ ተደርገው ሊቀርቡ የሚችሉ መሆናቸው ከፍተኛ ግርምትን የፈጠረ ሲሆን መንግስትም ክሱን ሊደግፍ የሚችል ሰነድ በሚፈልገው መልኩ መፈበርክ አለመቻሉንም አመላካች ሆኗል፡፡ ይህንንም ችግር ለመቅረፍና ሌሎች መረጃዎችን ለመፈብረክ ይመስላል በተደጋጋሚ ጊዜ ችሎቱ እየተቋረጠ ለአቃቤ ሕግ ጊዜ እየተሰጠው የሚገኘው፡፡ በአሁኑም እንደተለመደው ችሎቱ ሲቋረጥ ይሄን ታሳቢ በማድረግ መሆኑ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ችሎቱ ለሐምሌ 22 የተቀጠረ ሲሆን እስከ ሐምሌ 30 ድረስም 10 ቪዲዮዎች ይታያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አላሁ አክበር!

No comments:

Post a Comment